menu.png
Passwort vergessen ?

Manueller Vergleich



•••► •••►
Vers Amharic NT English: King James Version
1 ነገር ግን ከሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን ያዘጋጁትን ሽቱ ይዘው ከእነርሱም ጋር አንዳንዶቹ ወደ መቃብሩ እጅግ ማልደው መጡ። Now upon the first day of the week, very early in the morning, they came unto the sepulchre, bringing the spices which they had prepared, and certain others with them.
2 ድንጋዩንም ከመቃብሩ ተንከባሎ አገኙት፥ And they found the stone rolled away from the sepulchre.
3 ገብተውም የጌታን የኢየሱስን ሥጋ አላገኙም። And they entered in, and found not the body of the Lord Jesus.
4 እነርሱም በዚህ ሲያመነቱ፥ እነሆ፥ ሁለት ሰዎች የሚያንጸባርቅ ልብስ ለብሰው ወደ እነርሱ ቀረቡ፤ And it came to pass, as they were much perplexed thereabout, behold, two men stood by them in shining garments:
5 ፈርተውም ፊታቸውን ወደ ምድር አቀርቅረው ሳሉ፥ እንዲህ አሉአቸው። ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም። And as they were afraid, and bowed down their faces to the earth, they said unto them, Why seek ye the living among the dead?
6 የሰው ልጅ በኃጢአተኞች እጅ አልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል በሦስተኛውም ቀን ሊነሣ ግድ ነው እያለ ገና በገሊላ ሳለ ለእናንተ እንደ ተናገረ አስቡ። He is not here, but is risen: remember how he spake unto you when he was yet in Galilee,
8 ቃሎቹንም አሰቡ፥ ከመቃብሩም ተመልሰው ይህን ሁሉ ለአሥራ አንዱና ለሌሎች ሁሉ ነገሩአቸው። And they remembered his words,
10 ይህንም ለሐዋርያት የነገሩአቸው መግደላዊት ማርያምና ዮሐና የያዕቆብም እናት ማርያም ከእነርሱም ጋር የነበሩት ሌሎች ሴቶች ነበሩ። It was Mary Magdalene, and Joanna, and Mary the mother of James, and other women that were with them, which told these things unto the apostles.
11 ይህም ቃል ቅዠት መስሎ ታያቸውና አላመኑአቸውም። And their words seemed to them as idle tales, and they believed them not.
12 ጴጥሮስ ግን ተነሥቶ ወደ መቃብር ሮጠ፤ በዚያም ዝቅ ብሎ ሲመለከት የተልባ እግር ልብስን ብቻ አየ፤ በሆነውም ነገር እየተደነቀ ወደ ቤቱ ሄደ። Then arose Peter, and ran unto the sepulchre; and stooping down, he beheld the linen clothes laid by themselves, and departed, wondering in himself at that which was come to pass.
13 እነሆም፥ ከእነርሱ ሁለቱ በዚያ ቀን ከኢየሩሳሌም ስድሳ ምዕራፍ ያህል ወደሚርቅ ኤማሁስ ወደሚባል መንደር ይሄዱ ነበር፤ And, behold, two of them went that same day to a village called Emmaus, which was from Jerusalem about threescore furlongs.
14 ስለዚህም ስለ ሆነው ነገር ሁሉ እርስ በርሳቸው ይነጋገሩ ነበር። And they talked together of all these things which had happened.
15 ሲነጋገሩና ሲመራመሩም፥ ኢየሱስ ራሱ ቀርቦ ከእነርሱ ጋር ይሄድ ነበር፤ And it came to pass, that, while they communed together and reasoned, Jesus himself drew near, and went with them.
16 ነገር ግን እንዳያውቁት ዓይናቸው ተይዞ ነበር። But their eyes were holden that they should not know him.
17 እርሱም። እየጠወለጋችሁ ስትሄዱ፥ እርስ በርሳችሁ የምትነጋገሩአቸው እነዚህ ነገሮች ምንድር ናቸው? አላቸው። And he said unto them, What manner of communications are these that ye have one to another, as ye walk, and are sad?
18 ቀለዮጳ የሚባልም አንዱ መልሶ። አንተ በኢየሩሳሌም እንግዳ ሆነህ ለብቻህ ትኖራለህን? በእነዚህ ቀኖች በዚያ የሆነውን ነገር አታውቅምን? አለው። And the one of them, whose name was Cleopas, answering said unto him, Art thou only a stranger in Jerusalem, and hast not known the things which are come to pass therein these days?
19 እርሱም። ይህ ምንድር ነው? አላቸው። እነርሱም እንዲህ አሉት። በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ ስለ ነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ፤ And he said unto them, What things? And they said unto him, Concerning Jesus of Nazareth, which was a prophet mighty in deed and word before God and all the people:
20 እርሱንም የካህናት አለቆችና መኳንንቶቻችን ለሞት ፍርድ እንዴት አሳልፈው እንደ ሰጡትና እንደ ሰቀሉት ነው። And how the chief priests and our rulers delivered him to be condemned to death, and have crucified him.
21 እኛ ግን እስራኤልን እንዲቤዥ ያለው እርሱ እንደ ሆነ ተስፋ አድርገን ነበር፤ ደግሞም ከዚህ ሁሉ ጋር ይህ ከሆነ ዛሬ ሦስተኛው ቀን ነው። But we trusted that it had been he which should have redeemed Israel: and beside all this, to day is the third day since these things were done.
22 ደግሞም ከእኛ ውስጥ ማልደው ከመቃብሩ ዘንድ የነበሩት አንዳንድ ሴቶች አስገረሙን፤ Yea, and certain women also of our company made us astonished, which were early at the sepulchre;
23 ሥጋውንም ባጡ ጊዜ። ሕያው ነው የሚሉ የመላእክትን ራእይ ደግሞ አየን ሲሉ መጥተው ነበር። And when they found not his body, they came, saying, that they had also seen a vision of angels, which said that he was alive.
24 ከእኛም ጋር ከነበሩት ወደ መቃብር ሄደው ሴቶች እንደ ተናገሩት ሆኖ አገኙት፥ እርሱን ግን አላዩትም። And certain of them which were with us went to the sepulchre, and found it even so as the women had said: but him they saw not.
25 እርሱም። እናንተ የማታስተውሉ፥ ነቢያትም የተናገሩትን ሁሉ ልባችሁ ከማመን የዘገየ፤ Then he said unto them, O fools, and slow of heart to believe all that the prophets have spoken:
26 ክርስቶስ ይህን መከራ ይቀበል ዘንድና ወደ ክብሩ ይገባ ዘንድ ይገባው የለምን? አላቸው። Ought not Christ to have suffered these things, and to enter into his glory?
27 ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለ እርሱ በመጻሕፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጐመላቸው። And beginning at Moses and all the prophets, he expounded unto them in all the scriptures the things concerning himself.
28 ወደሚሄዱበትም መንደር ቀረቡ፥ እርሱም ሩቅ የሚሄድ መሰላቸው። And they drew nigh unto the village, whither they went: and he made as though he would have gone further.
29 እነርሱ። ከእኛ ጋር እደር፥ ማታ ቀርቦአልና ቀኑም ሊመሽ ጀምሮአል ብለው ግድ አሉት፤ ከእነርሱም ጋር ሊያድር ገባ። But they constrained him, saying, Abide with us: for it is toward evening, and the day is far spent. And he went in to tarry with them.
30 ከእነርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጦ ሳለ እንጀራውን አንሥቶ ባረከው፥ ቈርሶም ሰጣቸው፤ And it came to pass, as he sat at meat with them, he took bread, and blessed it, and brake, and gave to them.
31 ዓይናቸውም ተከፈተ፥ አወቁትም፤ እርሱም ከእነርሱ ተሰወረ። And their eyes were opened, and they knew him; and he vanished out of their sight.
32 እርስ በርሳቸውም። በመንገድ ሲናገረን መጻሕፍትንም ሲከፍትልን ልባችን ይቃጠልብን አልነበረምን? ተባባሉ። And they said one to another, Did not our heart burn within us, while he talked with us by the way, and while he opened to us the scriptures?
33 በዚያችም ሰዓት ተነሥተው ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፥ አሥራ አንዱና ከእነርሱ ጋር የነበሩትም። ጌታ በእውነት ተነሥቶአል ለስምዖንም ታይቶአል እያሉ በአንድነት ተሰብስበው አገኙአቸው። And they rose up the same hour, and returned to Jerusalem, and found the eleven gathered together, and them that were with them,
35 እነርሱም በመንገድ የሆነውን እንጀራውንም በቈረሰ ጊዜ እንዴት እንደ ታወቀላቸው ተረኩላቸው። And they told what things were done in the way, and how he was known of them in breaking of bread.
36 ይህንም ሲነጋገሩ ኢየሱስ ራሱ በመካከላቸው ቆሞ። ሰላም ለእናንተ ይሁን አላቸው። And as they thus spake, Jesus himself stood in the midst of them, and saith unto them, Peace be unto you.
37 ነገር ግን ደነገጡና ፈሩ መንፈስም ያዩ መሰላቸው። But they were terrified and affrighted, and supposed that they had seen a spirit.
38 እርሱም። ስለ ምን ትደነግጣላችሁ? ስለ ምንስ አሳብ በልባችሁ ይነሣል? And he said unto them, Why are ye troubled? and why do thoughts arise in your hearts?
39 እኔ ራሴ እንደ ሆንሁ እጆቼንና እግሮቼን እዩ፤ በእኔ እንደምታዩት፥ መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና እኔን ዳስሳችሁ እዩ አላቸው። Behold my hands and my feet, that it is I myself: handle me, and see; for a spirit hath not flesh and bones, as ye see me have.
40 ይህንም ብሎ እጆቹንና እግሮቹን አሳያቸው። And when he had thus spoken, he shewed them his hands and his feet.
41 እነርሱም ከደስታ የተነሣ ገና ስላላመኑ ሲደነቁ ሳሉ። በዚህ አንዳች የሚበላ አላችሁን? አላቸው። And while they yet believed not for joy, and wondered, he said unto them, Have ye here any meat?
42 እነርሱም ከተጠበሰ ዓሣ አንድ ቁራጭ፥ ከማር ወለላም ሰጡት፤ And they gave him a piece of a broiled fish, and of an honeycomb.
43 ተቀብሎም በፊታቸው በላ። And he took it, and did eat before them.
44 እርሱም። ከእናንተ ጋር ሳለሁ በሙሴ ሕግና በነቢያት በመዝሙራትም ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል ብዬ የነገርኋችሁ ቃሌ ይህ ነው አላቸው። And he said unto them, These are the words which I spake unto you, while I was yet with you, that all things must be fulfilled, which were written in the law of Moses, and in the prophets, and in the psalms, concerning me.
45 በዚያን ጊዜም መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው፤ Then opened he their understanding, that they might understand the scriptures,
46 እንዲህም አላቸው። ክርስቶስ መከራ ይቀበላል በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ይነሣል፥ And said unto them, Thus it is written, and thus it behoved Christ to suffer, and to rise from the dead the third day:
47 በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል። And that repentance and remission of sins should be preached in his name among all nations, beginning at Jerusalem.
48 እናንተም ለዚህ ምስክሮች ናችሁ። And ye are witnesses of these things.
49 እነሆም፥ አባቴ የሰጠውን ተስፋ እኔ እልክላችኋለሁ፤ እናንተ ግን ከላይ ኃይል እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ከተማ ቆዩ። And, behold, I send the promise of my Father upon you: but tarry ye in the city of Jerusalem, until ye be endued with power from on high.
50 እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው። And he led them out as far as to Bethany, and he lifted up his hands, and blessed them.
51 ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ። And it came to pass, while he blessed them, he was parted from them, and carried up into heaven.
52 እነርሱም፤ ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፥ And they worshipped him, and returned to Jerusalem with great joy:
53 ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ። And were continually in the temple, praising and blessing God. Amen.
7 Saying, The Son of man must be delivered into the hands of sinful men, and be crucified, and the third day rise again.
9 And returned from the sepulchre, and told all these things unto the eleven, and to all the rest.
34 Saying, The Lord is risen indeed, and hath appeared to Simon.