menu.png
Passwort vergessen ?

Manueller Vergleich



•••► •••►
Vers Amharic NT English: King James Version
1 በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ። Stand fast therefore in the liberty wherewith Christ hath made us free, and be not entangled again with the yoke of bondage.
2 እነሆ፥ እኔ ጳውሎስ እላችኋለሁ። ብትገረዙ ክርስቶስ ምንም አይጠቅማችሁም። Behold, I Paul say unto you, that if ye be circumcised, Christ shall profit you nothing.
3 ሕግንም ሁሉ እንዲፈጽም ግድ አለበት ብዬ ለሚገረዙት ሁሉ ለእያንዳንዶች ደግሜ እመሰክራለሁ። For I testify again to every man that is circumcised, that he is a debtor to do the whole law.
4 በሕግ ልትጸድቁ የምትፈልጉ ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋው ወድቃችኋል። Christ is become of no effect unto you, whosoever of you are justified by the law; ye are fallen from grace.
5 እኛ በመንፈስ ከእምነት የጽድቅን ተስፋ እንጠባበቃለንና። For we through the Spirit wait for the hope of righteousness by faith.
6 በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ፥ በፍቅር የሚሠራ እምነት እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና። For in Jesus Christ neither circumcision availeth anything, nor uncircumcision; but faith which worketh by love.
7 በመልካም ትሮጡ ነበር፤ ለእውነት እንዳትታዘዙ ማን ከለከላችሁ? Ye did run well; who did hinder you that ye should not obey the truth?
8 ይህ ማባበል ከሚጠራችሁ አልወጣም። ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉ ያቦካል። This persuasion cometh not of him that calleth you.
9 የተለየ ነገር ከቶ እንዳታስቡ እኔ በጌታ ስለ እናንተ ታምኜአለሁ፤ የሚያናውጣችሁ ማንም ቢኖር ግን ፍርዱን ሊሸከም ነው። A little leaven leaveneth the whole lump.
11 ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እስከ አሁን መገረዝን ብሰብክ እስከ አሁን ድረስ ለምን ያሳድዱኛል? እንኪያስ የመስቀል ዕንቅፋት ተወግዶአል። And I, brethren, if I yet preach circumcision, why do I yet suffer persecution? then is the offence of the cross ceased.
12 የሚያውኩአችሁ ይቆረጡ። I would they were even cut off which trouble you.
13 ወንድሞች ሆይ፥ እናንተ ለአርነት ተጠርታችኋልና፤ ብቻ አርነታችሁ ለሥጋ ምክንያትን አይስጥ፥ ነገር ግን በፍቅር እርስ በርሳችሁ እንደ ባሪያዎች ሁኑ። For, brethren, ye have been called unto liberty; only use not liberty for an occasion to the flesh, but by love serve one another.
14 ሕግ ሁሉ በአንድ ቃል ይፈጸማልና፥ እርሱም። ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የሚል ነው። For all the law is fulfilled in one word, even in this; Thou shalt love thy neighbour as thyself.
15 ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱ ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ። But if ye bite and devour one another, take heed that ye be not consumed one of another.
16 ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ። This I say then, Walk in the Spirit, and ye shall not fulful the lust of the flesh.
17 ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና፥ እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ፤ ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም። For the flesh lusteth against the Spirit, and the Spirit against the flesh: and these are contrary the one to the other: so that ye cannot do the things that ye would.
18 በመንፈስ ብትመሩ ግን ከሕግ በታች አይደላችሁም። But if ye be led of the Spirit, ye are not under the law.
19 የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፥ ርኵሰት፥ Now the works of the flesh are manifest, which are these; Adultery, fornication, uncleanness, lasciviousness,
20 መዳራት፥ ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥ Idolatry, witchcraft, hatred, variance, emulations, wrath, strife, seditions, heresies,
21 መለያየት፥ መናፍቅነት፥ ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም። Envyings, murders, drunkenness, revellings, and such like: of the which I tell you before, as I have also told you in time past, that they which do such things shall not inherit the kingdom of God.
22 የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው። But the fruit of the Spirit is love, joy, peace, longsuffering, gentleness, goodness, faith,
23 እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም። Meekness, temperance: against such there is no law.
24 የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ። And they that are Christ's have crucified the flesh with the affections and lusts.
25 በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ። If we live in the Spirit, let us also walk in the Spirit.
26 እርስ በርሳችን እየተነሣሣንና እየተቀናናን በከንቱ አንመካ። Let us not be desirous of vain glory, provoking one another, envying one another.
10 I have confidence in you through the Lord, that ye will be none otherwise minded: but he that troubleth you shall bear his judgment, whosoever he be.