menu.png
Passwort vergessen ?

Manueller Vergleich



•••► •••►
Vers Amharic NT English: King James Version
1 እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። I exhort therefore, that, first of all, supplications, prayers, intercessions, and giving of thanks, be made for all men;
3 ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው። For this is good and acceptable in the sight of God our Saviour;
5 አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ For there is one God, and one mediator between God and men, the man Christ Jesus;
6 ራሱንም ለሁሉ ቤዛ ሰጠ፥ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ፤ Who gave himself a ransom for all, to be testified in due time.
7 እኔም ለዚህ ነገር አዋጅ ነጋሪና ሐዋርያ በእምነትና በእውነትም የአሕዛብ አስተማሪ ለመሆን ተሾምሁ፤ እውነት እናገራለሁ፤ አልዋሽም። Whereunto I am ordained a preacher, and an apostle, (I speak the truth in Christ, and lie not;) a teacher of the Gentiles in faith and verity.
8 እንግዲህ ወንዶች በስፍራ ሁሉ አለ ቍጣና አለ ክፉ አሳብ የተቀደሱትን እጆች እያነሱ እንዲጸልዩ እፈቅዳለሁ። I will therefore that men pray every where, lifting up holy hands, without wrath and doubting.
9 እንዲሁም ደግሞ ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸልሙ፤ እግዚአብሔርን እንፈራለን ለሚሉት ሴቶች እንደሚገባ፥ መልካም በማድረግ እንጂ በሽሩባና በወርቅ ወይም በዕንቍ ወይም ዋጋው እጅግ በከበረ ልብስ አይሸለሙ። In like manner also, that women adorn themselves in modest apparel, with shamefacedness and sobriety; not with broided hair, or gold, or pearls, or costly array;
11 ሴት በነገር ሁሉ እየተገዛች በዝግታ ትማር፤ Let the woman learn in silence with all subjection.
12 ሴት ግን በዝግታ ትኑር እንጂ ልታስተምር ወይም በወንድ ላይ ልትሰለጥን አልፈቅድም። But I suffer not a woman to teach, nor to usurp authority over the man, but to be in silence.
13 አዳም ቀድሞ ተፈጥሮአልና፥ በኋላም ሔዋን ተፈጠረች። For Adam was first formed, then Eve.
14 የተታለለም አዳም አይደለም፥ ሴቲቱ ግን ተታልላ በመተላለፍ ወደቀች፤ And Adam was not deceived, but the woman being deceived was in the transgression.
15 ነገር ግን በእምነትና በፍቅር በቅድስናም ራሳቸውን እየገዙ ቢኖሩ በመውለድ ትድናለች። Notwithstanding she shall be saved in childbearing, if they continue in faith and charity and holiness with sobriety.
2 For kings, and for all that are in authority; that we may lead a quiet and peaceable life in all godliness and honesty.
4 Who will have all men to be saved, and to come unto the knowledge of the truth.
10 But (which becometh women professing godliness) with good works.